በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀነራል ብርሃኑ በሱዳን ጉዳይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር


ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

በሱዳን መንግሥት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች የሦስተኛ ወገን አጀንዳ ለማስፈጸም እየሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

“እየተላላከ ያለ” ሲሉ የገለፁት ቡድን የሱዳን እና የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ወዳልሆነ ነገር ለማስገባት እየሰራ ነው በማለት ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ አውሮፕላን የሱዳንን የአየር ክልል ጥሶ ገብቷል በሚል ከካርቱም ወገን የተሰነዘረውን ውንጀላም አጣጥለዋል።

“ወደ ጦርነት የምንገባ ከሆነም በግልፅ እንጅ በድብቅ አይሆንም” ሲሉም ነው ኢትዮጵያዊው ጄነራል ለአሜሪካ ድምፅ ያስረዱት።

የተሳሳተ ውሳኔ ወስነን ወደነሱ ወጥመድ እንድንገባ የሚፈልጉ ወገኖች አሉ ያሉት ጄነራል ብርሃኑ ጦርነት በፈለገ ትንሽ ቡድን ፍላጎት ግን ወደነሱ ቀለበት አንገባም ብለዋል።

ሰከን የማለትን አስፈላጊነት የጠቀሱት ኤታማዦር ሹሙ መሬታችን ደግሞ የትም አይሄድም በማለትም አክለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጀነራል ብርሃኑ በሱዳን ጉዳይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00


XS
SM
MD
LG