ዋሽንግተን ዲሲ —
ባሳለፍነው ሳምንት ወታደራዊና የደህነንት ሹም ሽር የተካሄደበት ሳምንት ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩት ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ተሸኝተው በቦታው ላይ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ተሾመዋል።
የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በነበሩት በአቶ ጌታቸው አሰፋ ምትክ ደግሞ ጄነራል አደም መሐመድ ተሾመዋል።
ከዚህ ሹም ሽር በተጨማሪ ወታደራዊ ማዕረጋቸው ተገፍፎ ከሠራዊቱ ተባርረው የነበሩትና ዘጠኝ ዓመት ታስረው የቆዩት የቀድሞው የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ብሪጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እና ማዕረጋቸው ተገፎ የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዣዥ ሜዠር ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ማዕረጎቻቸው ከነሙሉ ኮከቡ ተመልሶ ጡረታቸው እንዲከበርላቸው መወሰኑ ታውቋል።
ጽዮን ግርማ የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ብሪጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ለእሁድ ምሽት ፕሮግራም አወይታቸዋለች።
ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ