አዲስ አበባ —
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ገዳይ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ። አስር አለቃ መሳፍንት በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ የወሰነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
ይሁንና ቅጣቱ እንደከበደ የሚገልጹት የተከሳሽም ይሁን በሞት መቀጣት ነበረበት የሚሉት የከሳሽ ወገኖች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አልተቀበሉም፡፡ ሁለቱም አካላት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡ ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
ሰኔ 15/2011ዓ.ም ከምሽቱ 3ሰዓት ላይ የቀድሞውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና አብረዋቸው የነበሩትን ጓደኛቸውን ሜ/ጄኔራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሲከሰስ የቆየው የ10 አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መኮንን በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በግንቦት ወር 2011 ዓ/ም ወደ ጎንደር ከተማ በማቅናት፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የግድያ ወንጀሉ ጠንሳሽ እንደሆኑ በክሱ ከጠቀሳቸው ከብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ጋር ተገናኝቶ ተልዕኮ ስለመቀበሉ ክሱ ያስረዳል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።