በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሮፌሰር ገቢሣ ኤጄታ በኢትዮጵያ


የዩናይትድ ስቴትስ የሣይንስ ልዑክ ፕፎፌሰር ገቢሣ ኤጄታ
የዩናይትድ ስቴትስ የሣይንስ ልዑክ ፕፎፌሰር ገቢሣ ኤጄታ

የዩናይትድ ስቴትስ የሣይንስ ልዑክ ፕፎፌሰር ገቢሣ ኤጄታ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በትምህርት ማዳረስና ጥራት እንዲሁም በምግብ ዋስትና ጉዳዮች ላይ ተናግረዋል፡፡

ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት ፕሮፌሰር ገቢሣ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ትምህርትን ለማስፋፋት ያደረገውን ጥረት አሞግሰው እርምጃው ለዜጎች ብዙ ዕድል መክፈቱን ተናግረዋል።

ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ከተማሪዎች ጋር ባደረጉት ጥልቅ ውይይት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት አሣሣቢ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር ገቢሣ በውጪ ከሚገኙና ብቃት ካላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ስምምነት በማድረግ መምህራንን በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች በአስቸኳይ ማሰልጠንን እንደ መፍትሔ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል በአጭር ጊዜ ማሣካት ከባድ እንደሆነ የገለፁት ፕሮፌሰር ገቢሣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በዚህ ረገድ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል።

ይሁን እንጂ አገሪቱ ሰፊ እንደመሆንዋ መንግሥት ሁሉንም የትምህርና የልማት ተግባሮች በራሱ ማከናወን ስለማይችል አማራጩ ለግሉ የኢኮኖሚ ዘርፍ በቂ ዕድል መፍጠር እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ፕሮፌሰር ገቢሣ ኤጄታ ለመለስካቸው አምኃ የሰጡትን ዝርዝር ቃለ ምልልስ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG