ሃያ አንድ የሚሆኑ የካንሰር ታማሚዎች በጦርነት በመፈራረስ ላይ ካለችው የጋዛ ሰርጥ፣ ከረም ሻሎም በተባለው መሻገሪያ በኩል ግብፅ መግባታቸውን አንድ የሕክምና አገልግሎት ምንጭ ተናግረዋል።
የካንሰር ታማሚዎቹ ለሕክምና ወደ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እንደሚላኩ፣ ማንንነታቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉት ምንጭ ለኤኤፍፒ ወኪል ተናግረዋል።
በፍልስጤማውያኑ በኩል ያለው የራፋ መተላለፊያ ባለፈው ግንቦት መጀመሪያ ላይ በእስራኤል ኃይሎች ከተዘጋ ወዲህ የተደረገ የነፍስ አድን ሥራ እንደሆነም ታውቋል።
የራፋ መተላለፊያን መልሶ ለመክፈት የተደረገው ድርድር ሳይሳካ ቀርቷል። በፍልስጤማውያኑ በኩል ያለው የራፋ መተላለፊያ በእስራኤል ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እስካለ ድረስ ሰዎችን የማስወጣቱን ሥራ እንደማትቀጥል ግብጽ አስታውቃለች፡፡
ባለፉት ስምንት ወራት በተካሄደው ጦርነት 37 ሺሕ 765 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸውን በሃማስ የአስተዳደር ግዛት ውስጥ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም