በሐማስ በተመራዉና በእስራኤል ላይ በተፈፀመው ጥቃት ምክንያት የተጫረው ጦርነት አንድ ዓመት ባስቆጠረበት በዚህ ወቅት፣ በሌባኖስ ድንበር ላይ በእስራኤል እና በሄዝቦላ መካከል የሚካሄደው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል። ግጭቱ አዲስ የስብዓዊ ቀውስ ያስከተለ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው ደግሞ፣ 200 ሺሕ ሰዎችን አፈናቅሏል።
ኤተል ቦኔት ከደቡብ ሌባኖስ የላከችውንና በኤሊዛቤት ቸርነፍ የተተረከውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።
መድረክ / ፎረም