ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አማካይ የነዳጅ ዋጋ ከአምስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊትር ከ1 ዶላር አካባቢ መሆኑ ተገለፀ።
ትሪፕል ኤ የሚባለው የአሜሪካ ተሽከርካሪዎች ማኅበር በብሄራዊ ደረጃ አማካይ የነዳጅ ዋጋ ካለፈው ሣምንት ጋር ሲነፃፀር በአሥራ አምስት ሣንቲም ቀንሶ ዛሬ መደበኛው ቤንዚን በሊትር 1 ዶላር ከ 05 ሣንቲም መሆኑን አስታውቋል።
የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ሰኔ አጋማሽ አንድ ጋለን ቤንዚን ወደ 5 ዶላር ወይም ሊትሩ ወደ 1 ዶላር ከ32 ሣንቲም አሻቅቦ የነበረ ሲሆን በካሊፎርኒያና ሃዋይኢ አሁንም ጋሎኑ ከ5 ዶላር በላይ ሆኖ እንደቀጠለ ነው።
አንድ ጋሎን 3.78 ሊትር ነው።