በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋብምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ዕጩ አዳማ ባሮው አሸንፈዋል


የተቃዋሚ ዕጩ አዳማ ባሮው
የተቃዋሚ ዕጩ አዳማ ባሮው

ጋምቢያ ውስጥ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ዕጩ አዳማ ባሮው የረጅም ጊዜውን የሀገሪቱን መሪ ያህያ ጃሜህን እንዳሸነፉ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ።

ባሮው ከተሰተው ድምፅ አርባ አምስት ከመቶውን ማለትም 26ሺሕ 3መቶ ድምፅ ሰላሣ ሁለት ከመቶ ሲያገኙ ፕሬዚደንቱ ጃሜ 212.000 ሶስተኛ ዕጩ ማማ ካንዴህ አስራ ሰባት ከመቶውን አግኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜ በተቃዋሚ ዕጩው መሸነፋቸውን አምነው እንደተቀበሉ የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀ መንበር አሊዩ ሞማር ጃይ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል ።
ጃሜህ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ቆይተው ሲያበቁ አሁን መሸንፋቸውን መቀበላቸው በጣም ለየት ያለ ርምጃ ነው ብለዋል።
ከፕሬዚዳንቱ በኩል ለጊዜዉ የወጣ መግለጫ የለም።
በዋና ከተማዋ ባንጁል ህዝቡ በተቃዋሚው አዳማ ባሮው ማሸነፍ ተደስቶ ሲጨፍር መዋሉን አልፋ ጃሎው ለቪኦኤ ዘግቧል።
የሃምስ ኦንድ ዓመቱ ባሮው በትናንቱ ምርጫ ያህያ ጃሜህን የተፎካካረውን የሰባት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት ወክለው ነው የተወዳደሩት።
እሳቸውም የሃማሳ እንድ ዓመት ሰው የሆኑት ያህያ ጃሜ በ1994ዓ.ም. በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ጨብጠው ሲያበቁ ከዚያ በኋላ በተካሄዱ እና ተቺዎች
"ነፃም ፍትሃዊም ያልነበሩ" ባሉዋችዉ ምርጫዎች እያሸነፉ እስካሁን ትንሿን የምዕራብ አፍሪካ ሃገር ሲገዙ ኖረዋል።
የመብት ተሟጋች ቡድኖች ፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውንና ጋዜጠኞችን ያስራሉ፣ ኣለያም ይገድላሉ ብለው በተደጋጋሚ ሲወነጅሉዋቸው ቆይተዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሺናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ
"መጪው መንግሥት የጋምቢያን የሠብዓዊ መብት ይዞታ ማሻሻል የፖለቲካ እስረኞችን መፍታትና እና አፋኝ ሕጎችን መስረዝ ይጠበቅባቸዋል” ሲል አሳስበዋል።
በምርጫው የሚያሸንፉ መስሉዋቸው የነበሩት ጃሜህ ከምርጫው በኋላ የተቃውሞ ሠልፍ የሚባል አይፈቀድም ሲሉ አውጀው ነበር።

XS
SM
MD
LG