በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋምቢያው የሕያ ጃሜ እየተገፉ ነው


የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ
የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ

የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ መንበረ ሥልጣኑን ተቆጣጥረው ለመቆየት ያደረጉት ውሣኔ ላይሠምርላቸው እንደሚችል ተነግሯል።

ጋምቢያ ከጥቂት ሣምንታት በፊት አድርጋ በነበረ ምርጫ የተቀማጩ ፕሬዚዳንት ተቀናቃኝና ተፎካካሪ የነበሩት አዳማ ባሮ ማሸነፋቸው በይፋ ተነግሯል።

ከውጤቱ በኋላ ለአሸናፊው የደስታ መግለጫ አሰምተው የነበሩት፤ የምርጫውን ውጤትም እንደሚያከብሩ የተናገሩት በዚህም ምክንያት ከግራም ከቀኝም ሙገሣ የጎረፈላቸው ፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ ውዲያው ሃሣባቸውን ቀየሩና ውጤቱን እንደማይቀበሉ ደግሞ አሣውቁ።

በዚያ አቋማቸው ብዙ ሰው ተከፋ፤ ጎረቤቶቻቸውም ሆኑ ጫና የሚኖራቸው የመሰሉ የራቁም ሃገሮች ተረባረቡ።

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ለአሸናፊውና ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ለአዳማ ባሮ ዕውቅና ሰጠና ጃሜ ፈጥነው መንበረ ሥልጣኑን እንዲያስረክቡ መወትወት ያዘ።

አደማ ባሮው
አደማ ባሮው

ለማንኛውም የፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ የምርጫውን ውጤት ለመሠረዝ የደረሱበት ውሣኔ በሕግ አግባብ እንዲያዝ ታሰበና ከናይጀርያና ከሲየራ ሌኦን የተውጣጡ አምስት ዳኞች የሚሰየሙበት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እንዲያየው ለዛሬ፣ ማክሰኞ ጥር 2/2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ተያዘ።

ይሁን እንጂ ዳኞቹ ዛሬ ጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል ሳይገቡ ቀርተዋል።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የጋምቢያው የሕያ ጃሜ እየተገፉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00

XS
SM
MD
LG