በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል ፒኖ በተባለ ቀበሌ 29 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ


በጋምቤላ ክልል ፒኖ በተባለ ቀበሌ 29 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00

በጋምቤላ ክልል ፒኖ በተባለ ቀበሌ 29 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

በጋምቤላ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋራ በተገናኘ፣ ፒኖ በተባለ ቀበሌ፣ 29 ሰዎች እንደተገደሉ፣ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ተናገሩ፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት አቶ ኡሞድ አግዋ የተባሉ የአካባቢው ተወላጅ፣ በቀበሌው፣ መንደሮችን የማቃጠል እና የመዝረፍም ተግባራት እንደተፈጸሙ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከጋምቤላ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስተያየት ለማግኘት፣ የአሜሪካ ድምፅ ያደረገው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ የጽ/ቤቱ ሓላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ፣ ትላንት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ግን፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የተጀመረው ግጭት፣ የብሔር መልክ ይዞ ወደተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደተዛመተና በዚኽም ዐያሌ ሰዎች እንደተገደሉ፣ ብዙዎችም እንደተፈናቀሉ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው እናት ፓርቲ ደግሞ፣ መንግሥት፣ በጋምቤላ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት የማስቆም ሓላፊነቱን እንዲወጣ፣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤም፣ በጋምቤላ ክልል ያለው የጎሣ ግጭት፣ በቂ ትኩረት እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠው አሳስቧል፡፡

በግጭቱ ዙሪያ አስተያየት የሰጡን አንድ ባለሞያ፣ በክልሉ እያጋጠመ ያለው ችግር፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መንሥኤ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG