በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በታጣቂዎች ተገደሉ


በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በታጣቂዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:29 0:00

በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በታጣቂዎች ተገደሉ

የጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ፣ በታጣቂዎች እንደተገደሉና አንድ የፖሊስ አባል መቁሰሉን፣ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

ትላንት እሑድ፣ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት፣ የማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዮት ሮኬት በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ የጋምቤላ ክልል ጸጥታ እና ሰላም ግንባታ ቢሮ ምክትል ሓላፊ ኡቶው ኡኮት ገልጸዋል፡፡

ኢንስፔክተር አብዮት፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋራ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቴፒ ከተማ የነበራቸውን ሥልጠና አጠናቀው፣ በተሽከርካሪ ወደ ጎደሬ ወረዳ እያቀኑ በነበረበት ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ፣ ጥቃት መፈጸሙን፣ አቶ ኡቶው አስረድተዋል።

የጥቃት ፈጻሚዎቹ ማንነት አለመታወቁንና አንድ የፖሊስ አባልም በጥቃቱ ስለ መቁሰሉ፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አክለው ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሓላፊ ምክትል ኢንፔክተር ኦቦንግ ኦዶንግ፣ እንዲህ ዐይነት ጥቃት በአካባቢው የተፈጸመው፣ ከሦስት ዓመት በፊት እንደነበረ ጠቅሰው፣ በዚያ ጥቃትም፣ አንድ የወረዳው የግብርና ባለሞያ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስታወሰዋል።

በትላንቱ ጥቃት የተገደሉት የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዮት ሮኬት፣ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ በዛሬው ዕለት በጎደሬ ወረዳ መፈጸሙን፣ ኢንስፔክተር ኦቦንግ ኦዶንግ አስታውቀዋል፡፡

የጥቃት ፈጻሚዎቹን ማንነት ለማወቅና ወደ ሕግ ለማቅረብ፣ የጎደሬ እና የቴፒ ወረዳዎች ፖሊስ ጽሕፈት ቤቶች፣ በጋራ እየሠሩ እንደኾነም፣ ኢንስፔክተር ኦቦንግ አክለው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG