በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢታንግ ልዩ ወረዳ ግጭት 11 ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ


በኢታንግ ልዩ ወረዳ ግጭት 11 ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

በኢታንግ ልዩ ወረዳ ግጭት 11 ሰዎች ሲገደሉ በሺሕዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ባለፈው እሑድ፣ በታጣቂዎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች መካከል በተከሠተ ግጭት 11 ሰዎች መገደላቸውን፣ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

በግጭቱ፣ ስምንት የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ሲገደሉ፣ ሦስት የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች ሕይወት ማለፉን የቢሮው ሓላፊ አቶ ባጓል ጆክ አስታውቀዋል፡፡

የተቃዋሚው የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ በበኩሉ፣ በግጭቱ ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ፣ ከ15ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ ደግሞ፣ በግጭቱ ምክንያት ከ10ሺሕ በላይ ሕዝብ ተፈናቅሏል፤ እገዛ ለማድረግም ርዳታ እያፈላለግን ነው፤ ብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG