የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት፣ በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከሥቶ ከነበረው የጸጥታ መደፍረስ ጋራ በተያያዘ፣ ግንኙነት ነበራቸው ብሎ የጠረጠራቸውን 14 የአመራር አባላት እና አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡
የጋምቤላ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች፣ ከዞን እስከ ወረዳ ባሉ የአስተዳደር መዋቅሮች ውስጥ የነበሩ አመራሮች መኾናቸውን ጠቅሰው፣ ጉዳያቸውም በሕግ ተይዟል፤ ብለዋል፡፡
በጋምቤላ ግጭቶች ላይ ጥናት ያደረጉ አንድ ባለሞያ ደግሞ፣ እንዲህ ዓይነት ርምጃዎች፣ ጊዜያዊ መፍትሔን እንጂ ዘላቂ ሰላምን እንደማያመጡ አመልክተዋል፡፡ ችግሩ መፈታት ያለበት፣ በፖለቲካዊ ንግግር እና በሕዝባዊ ውይይት እንደኾነም ይመክራሉ፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም