አምቦ —
በጋምቤላ ክልል ለፀጥታ ስጋት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን ከ30 ሰዎች በላይ ይዞ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው ሀላፊ አቶ ቶማስ ቱት ለቪኦኤ እንዳሉት "ከነዚው መካከል የህወሓት ወታደሮች፣ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) እንዲሁም የኦነግ ሸኔ አባላት እንደሆኑ ተጠርጥረዋል" ብለዋል።
አቶ ቶማስ "ጋምቤላ ውስጥ አሁን አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም መንግሥት መተኛት የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል። ክልሉ ለሚያነሳው ወቀሳ ስማቸው የተጠቀሱትን ቡድኖች አመራሮች አግኝተን በስልክ ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለአሁኑ አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡