በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ በጋምቤላ የተፈጸመን የመንገደኞች ግድያ እያጣራሁ ነው አለ


ኢሰመኮ በጋምቤላ የተፈጸመን የመንገደኞች ግድያ እያጣራሁ ነው አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:23 0:00

ኢሰመኮ በጋምቤላ የተፈጸመን የመንገደኞች ግድያ እያጣራሁ ነው አለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን/ኢሰመኮ/፣ ባለፈው ረቡዕ፣ በጋምቤላ ክልል በታጣቂዎች ተፈጸመ የተባለውን የመንገደኞች ግድያ ማጣራት መጀመሩን ገለጸ።

በኮሚሽኑ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በጥቃቱ የሰዎች ሞት እና ጉዳት መረጃ ደርሶናል፤ ጉዳዩን ማጣራትም ጀምረናል፤ ብለዋል።

የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በበኩሉ፣ ከጥቃቱ ጋራ በተያያዘ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።

በመንገደኞች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ፣ ብሔር ተኮር ግጭት ይነሣል፤ የሚል ስጋት ያደረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ፣ መንግሥት ሰላምን እንዲያሰፍን ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG