በጋምቤላ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከሰተው የኮሌራ ወርረሽኝ 15 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት “ባለፈው ሳምንት በኑዌር ዞን የተከሠተው በሽታ በላቦራቶሪ ምርመራ ኮሌራ መሆኑ ተረጋግጧል” ብለዋል። እስከ ዛሬ ድረስ በተደረገው ማጣራትም 15 ሰዎች ሲሞቱ 306 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን አስታውቀዋል።
በሽታው መጀመሪያ የተከሰተበት የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ የሟቹን ቁጥር 18 አድርሶታል።
የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጋትቤል ግርማል፣ የሟቾቹ ቁጥር መጨመሩን እና የታማሚዎቹ ቁጥር ደግሞ 270 መኾኑን ገልጸዋል።
በደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆነው አኮቦ ወረዳ በሽታው መከሰቱን የጠቆሙት አቶ ጋትቤል በወረዳው የስልክ አገልግሎት ችግር በመኖሩ መረጃ ከተለዋወጡ ሦስት ቀናት ማለፉን አስታውቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም