የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የ34 ዓመቱን የትምህርት ሚኒስትራቸውን ገብርኤል አታልን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው አድርገው ሾሙ።
ማክሮን የአውሮፓ ፓርላማን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት የያዙት ጥረት አካል ተደርጎ ታይቷል።
እርምጃው አይነተኛ የፖለቲካ ለውጥ ባያመጣም ማክሮን ባለፈው አመት የወሰዱት የጡረታ እና የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ከፈጠረው ሁኔታ ለመሻገር እና በሰኔው የአውሮፓ ህብረት ምርጫ ለማዕከላዊ አቋም አራማጁ ፓርቲያቸው እድሉን ለማስፋት መፈለጋቸውን ያሳያል ተብሏል።
የመራጭ አስተያየት መመዘኛዎች የማክሮን ጎራ ከሩቅ ቀኝ ዘመሟ መሪ መሪን ፓርቲ ለፔን ፓርቲ በስምንት በመቶ ነጥብ ይከተላል።
የማክሮን የቅርብ ሰው የሆኑት አታል ተሰናባቿን የረዥም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሊዛቤጥ ቦርንን ይተካሉ።
መድረክ / ፎረም