በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሊ ቦንጎ ወደ ውጪ መጓዝ እንደሚችሉ ተገለጸ


በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወግደው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የጋቦኑ መሪ አሊ ቦንጎ
በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወግደው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የጋቦኑ መሪ አሊ ቦንጎ
- ከቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ጋራ ፍኖተ ካርታ ለመንደፍ ስምምነት ላይ ተደርሷል
በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወግደው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የጋቦኑ መሪ አሊ ቦንጎ፣ የመንቀሳቀስ እና ወደ ውጪ የመጓዝ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ ተገለፀ።
የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ እና ባለፈው ሰኞ የሀገሪቱ የሽግግር ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙት ጀኔራል ብሪስ ንግዌማ፤ ዛሬ ባወጡት መግለጫ “የመንቀሳቀስ መብታቸው የተጠበቀ ነው፣ ካሻቸውም ወደ ውጪ መጓዝ ይችላሉ” ብለዋል።
ከአባታቸው ሥልጣኑን ወርሰው ለ14 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት አሊ ቦንጎ፣ ፓርቲያቸው ምርጫ ባሸነፈ አንድ ሰዓት ውስጥ ነበር በተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በቁም እስር ስር ላይ የዋሉት። መፈንቅለ መንግሥቱ ካለ ደም መፋሰስ የተካሄደ እንደሆነ ይነገርለታል።
“የጤናቸውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የቀድሞው ፕሬዚደንት የመንቀሳቀስ መብት አላቸው”
“የጤናቸውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የቀድሞው ፕሬዚደንት የመንቀሳቀስ መብት አላቸው” ብለዋል ግዜያዊው ፕሬዝደንት ንግዌማ፡፡
አሊ ቦንጎ በእ.አ.አ 2018 በተከታታይ ባጋጠማቸው የአንጎል ውስጥ የደም ሥር መዘጋት ወይም ስትሮከ፤ ሰውነታቸውን፣ በተለይም የቀኝ እግራቸውንና የቀኝ እጃቸውን የማንቀሳቀስ ውስንነት ገጥሟቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (በእንግሊዘኛ ምዕጻሩ ኢካስ) እና የጋቦን መፈንቅለ መንግሥት መሪዎች፣ ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመመለስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለመንደፍ መስማማታቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።
ኢካስ፤ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት የሆኑትን ፋውስቲን ትዋዴራን ልዑክ በማድረግ ወደ ጋቦን ልኮ ነበር። ሁለቱ ወገኖች ፍኖተ ካርታውን ለመንደፍ መስማማታቸውን አንድ ባለሥልጣን ቢያረጋግጡም፣ ሁለቱም ወገኖች ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG