ጅግጅጋ —
ባለፈው ዓመት ሐምሌ 28 /2010 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ መሀመድ ኡመር ስምሪት የተሰጣቸው ናቸው በሚል የሚጠረጠሩትና “ሄጎ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ወጣቶች በከተማው ነዋሪዎች ላይ አደረሱት የተባለው አንድ ዓመት ሞላው።
በወቅቱ ይፋ በተደረገው ሪፖርት ሰባት አብተ ክርስትያናት ተቃጥለዋል፤ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፤ ንብረት ወድሟል እንዲሁም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሃብትም ተዘርፏል። በወቅቱ ጥቃቱ በደረሰ ጊዜ ጉዳዩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ቢሮ ድረስ በመሄድ አቤቱታ ከማቅረብ ጀምሮ ኮሚቴ እንዲቋቋምና ተጎጂዎች እንዲረዱ ያደረገ ወጣት የዛሬ የጋቢና እንግዳችን ነው። ጂጂጋ ተወልዶ ያደረገውና ኑሮውን በአዲስአበባ ያደረገው ሱራፌል ጥላዬ ለሌሎች ወጣቶች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር አከናውኗል ሲሉም ሌሎች ምስክርነት ይሰጡለታል። አዲስ ቸኮል ለጋቢና ቪኦኤ የዘጋቢዎች መስኮት ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው የጽምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ