በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን ሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች ከሰሜን ኢትዮጵያ የሚወጡት ዘገባዎች እንዳሳሰባቸው ገለጹ


የቡድን ሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች ከሰሜን ኢትዮጵያ የሚወጡት ዘገባዎች እንዳሳሰባቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00

የቡድን ሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች ከሰሜን ኢትዮጵያ የሚወጡት ዘገባዎች እንዳሳሰባቸው ገለጹ

ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ኤምባሲዎች “አከራካሪ” ከተባሉት ከሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚወጡት የግጭት ዘገባዎች እንዳሳሰቧቸው ገለፁ። ኤምባሲዎቹ ቅዳሜ ዕለት በጋራ ባወጡት አጭር መግለጫ፣ ውስብስብ ፖለቲካዊ እና የደኅንነት ቀውስን ለመፍታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ሁሉንም ያካተተ ውይይት ማድረግ ብቸኛ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል።

በተያያዘ፣ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ/ ዩኤን-ኦቻ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ባወጣው ሪፖርቱ፣ በራያ አላማጣ ወረዳ እና አካባቢዎቹ ዳግም ባገረሸው ግጭት፣ 29ሺሕ ሰዎች ወደ ሰሜን ወሎ እና ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞኖች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

ተፈናቃዮቹ፣ አሳሳቢ የምግብ እና የውኃ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው ሪፖርቱ ገልጾ፣ አፋጣኝ ድጋፍ ለማድረስ ከአጋር ድርጅቶች ጋራ እንቅስቃሴ እያደረገ መኾኑን አመልክቷል፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ተፈናቃዮች፣ በአሳሳቢ የምግብ እና የማረፊያ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ለተደጋጋሚ መፈናቀል ምክንያት ለኾነው የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ መንግሥት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG