በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የG20 አገሮች መሪዎች በቶሮንቶ ካናዳ ተሰባሰቡ


የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል

ስምንት በኢኮኖሚ ከበርቴ የሆኑ እና ኢኮኖሚያቸዉ እየመጠቀ ያለ እንደ ቻይናና ህንድ ያሉ ታዳጊ አገሮችን የጠቀለለ የ G 20 መሪዎች ጉባኤ በቋፍ ያለ የዓለም ኢኮኖሚ አሁንም ማነቃቂያ እንደሚያሰፈልገውና የበጀት ኪሳራቸውን ለመቀነሰ ግን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተስማምተዋል።

ጉባኤዉን ባስተናገደችው አገር ካናዳ ባቀረበችው እቅድ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ስቲቨን ሀርፐር የኢኮኖሚ ተሃድሶው እንዲቀጥል፣ አገሮች ባለፈዉ ዓመት ጉባኤ በፒትስበርግ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ፣ የዓለም ገበያን ለማረጋጋት መሪዎቹ የተቀነባበረ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

የG 20 አገሮች የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል።

የG20 እና G8 መሪዎች በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ያወጡት መግለጫ በአያሌ አገሮች የስራ አጡ ህዝብ ቁጥር ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ስለሆነ፣ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ማገገም በቋፍ ያለና ኑሮ ላይ ያስከተለው ቀውስም እንደሃገሮቹ የተለያየ ነው ይላል።

የግል ንግዶችን የብድር ፍላጎት ለማሙዋላትና ኢኮኖሚውን እንደገና ለማንሰራራት የማነቃቂያ እርምጃ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸዉ ተጠቅሷል።

በዓለም እኩል የማይራመዱና ወጣ ገባ የኢኮኖሚ አያያዞች፣ በተለይም የአገሮች የባጄት ኪሳራ ወደ ማገገም የተያዘዉን አቅጣጫም ሊቀለብሱ እንደሚችሉ የG20 መሪዎች ይናገራሉ።

ፕሬዚደንት ኦባማና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት፣ የኢኮኖሚ እድገቱ አንድ ተጨባጭ ውጤት ሳያሳይ፣ በመንግስታት የሚወሰዱ የማነቀቂያ እርምጃዎች እንዳይቋረጡ ፣ ያ ከሆነ ግን እንደገና የዓለም ዋጋ ግሽበት እንደሚከስት ያስጠነቅቃሉ።

በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ በዚህ ነጥብ ላይ ስላለዉ የሃሳብ ልዩነት ፕሬዚደንት ኦባማ ተጠይቀዉ በተለያዩ አገሮች የሚታየው የኢኮኖሚ ማገገም አሁንም በቋፍ ያለ እንደሆነና ተሃድሶ ላይ ለመድረስም ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። የጉባኤዉ መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የምትከተላችውን ልዩ ልዩ ፖሊሲዎች ያንጸባርቃል የሚሉት ፕሬዚደንት ኦባማም ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ የማንፈልግ ከሆነ ግን “በመካከለኛና ረጅም ጊዜያት በመተመን ከባድ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ መጋፈጥ ይኖርብናል፤” ይላሉ።

የሚቀጥለዉ የG 20 መሪዎች ጉባኤ በመጪው ህዳር ወር በሶል ደቡብ ኮሪያ ይደረጋል።

XS
SM
MD
LG