በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን ሃያ አባል ሃገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ በጣሊያን


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የቡድን ሃያ አባል ሃገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ ጣሊያን ውስጥ ተከፍቷል። የጉባኤው ተካፋዮች ከሚነጋገሩባቸው አጀንዳዎች መካከል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ዋስትና ይገኙባቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ እአአ ከ2019 ወዲህ በአካል ሲሰባሰቡ ይህ ጣልያን ማቴራ ከተማ ላይ የተከፈተው የመጀመሪያቸው ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲወገድ ክትባቱን በተጨማሪ የዓለም አካባቢዎች ማዳረስ ይኖርብናል፣ ይህን የጤና ቀውስ ለማክተም ቁልፉ በትብብር መስራት ነው ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶችን ለባለዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ሃገሮች ለማዳረስ የሚሰራውን ተቋም የኮቫክስ ወጪ ለመጋራት እያደረገች ያለውን አስተዋጽኦ አንስተዋል። ጣሊያን ኮቪድ-19ን ከጉባኤው መነጋገሪያ አጀንዳዎች መካከል በማድረጓም አሞግሰዋል።

ባለፉት ጥቂት ወራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ ከአጋሮችዋ ጋር ያላትን ትብብር የሚያጠናክር የውጭ ፖሊስ አቅጣጫ እየቀየሱ መሆናቸው ይስተዋላል።

በዚህም መሰረት ሚኒስትር ብሊንከን ኮቪድ-19ኝን ለመሳሰሉ የጋራ ጉዳዮች መፍትሄ ለማምጣት አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው እንደሚያሳስቡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከቱ ጉዳዮች እና ዘላቂነት እና አሳታፊ በሆነ መነግድ የዓለም ኢኮኖሚን እንዲያንሰራራ ጉዳዮችም በጋራ የቡድኑ አባል ሃገሮች በትብብር እንዲሰሩ ብሊንክን እንደሚያበረታቱ ተገልጿል።

በዛሬው የቡድን ሃያ አባል ሃገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባዔ በአፍሪካ የሴቶች እኩልነት እና ለወጣቶች መፈጠር ያለባቸውን ዕድሎች ጨምሮ በኢኮኖሚ ልማት ጉዳዮች እንዲሁም በሰብዓዊ ረድዔት ጥረቶችና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG