በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጂ 20 አባል አገሮች በአፍጋኒስታን ጉዳይ ዛሬ ይመክራሉ


ፎቶ ፋይል፦ የጂ 20 የባህል ሚኒስትሮች ስብሰባ ሐምሌ 29 ቀን 2021 ጣሊያን
ፎቶ ፋይል፦ የጂ 20 የባህል ሚኒስትሮች ስብሰባ ሐምሌ 29 ቀን 2021 ጣሊያን

የሰብአዊና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የምትገኘውን አፍጋኒስታንን አመስልከቶ የጂ 20 የበለጸጉ አገራት መሪዎች፣ ዛሬ ማክሰኞ በድረ ገጽ ይወያያሉ፡፡

መሪዎቹ ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ በአገሪቱ ስላለው የደህንነት ሁኔታና ስለሚያስፈልገው እርዳታም እንደሚመክሩ ተገልጿል፡፡

ስብሰባውን ያዘጋጁት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ሲሆኑ፣ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሪንድራ ሞዲ እንዲሁም ከአውሮፓ የጂ 20 አባል አገሮች በስብሰባው ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG