በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሣይ ጦር ከኒዤር መውጣት ጀመረ


የፈረንሳይ ጦር ከኒዤር ለመውጣት ሲዘጋጁ ኒያሚ፣ እአአ ጥቅምት 10/2023
የፈረንሳይ ጦር ከኒዤር ለመውጣት ሲዘጋጁ ኒያሚ፣ እአአ ጥቅምት 10/2023

የኒዤር ሁንታ በጠየቀው መሠረት፣ የፈረንሳይ ጦር ሀገሪቱን ጥሎ መውታት ጀምሯል። ፈረንሳይ ግጭት በሚያብጠው የምዕራብ አፍሪካ ሳህል ቀጠና የነበራትን ተጽእኖ የሚያዳክም ርምጃ ነው ተብሏል።

ሰኞ ዕለት፤ ሁንታው፣ የፈርሣይ ጦር ማክሰኞ መውጣት እንደሚጀምር ማስታወቁን ተከትሎ፣ በመዲናዋ ኒያሜይ ዙሪያ ባሉ አቧራማ መንገዶች ላይ የፈረንሣይ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መስተዋላቸውን የሮይተርስ ዜና ወኪል ከስፍራው ዘግቧል።

ወታደራዊው መንግስት፣ የፈረንሣይ ጦር በሚለቅበት ወቅት ሕዝቡ እንዲተባበር ጥሪ አድርጓል። 1ሺሕ 500 የሚሆኑት ወታደሮች ወደ ቻድ እንደሚጓዙ እና በመቶ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠረው ጉዞ፣ እንዳንዴም አስጊ በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ እንደሚደረግ ተመልክቷል።

በደርዘን የሚቆጠሩ የፈረንሣይ ወታደሮች ሰኞ ዕለት በወታደራዊ አውሮፕላን ለቀው መውጣታቸውን አንድ የአየር ማረፊያው ሠራተኛ እና ሁለት ሌሎች ምንጮች ማስታወቃቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ወታደራዊው አገዛዝ በኒዤር የሚገኙት የተባበሩት መንግስታትት አስተባባሪ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ትዕዛዙ የመጣው አሜሪካ ለሀገሪቱ የምታደርገውን የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታቋርጥ ማስታወቋን ተከትሎ ነው።

የተመድ የሰብዓዊ አስተባባሪ የሆኑት ሉዊዝ ኦቢን፣ ኒያሜይን በ72 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መታዘዙን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ መግለጫ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG