በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኖርማንዲ ውስጥ በእስረኞች ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት 2 የፈረንሳይ የማረሚያ ቤት ሰራተኞች ተገደሉ


የትራፊክ አደጋ የፖሊስ መኮንኖች ጥቃቱ በደረሰበት ሥፍራ በሥራ ላይ ሰሜናዊ ፈረንሳይ፣ እአአ ግንቦት 14/2024
የትራፊክ አደጋ የፖሊስ መኮንኖች ጥቃቱ በደረሰበት ሥፍራ በሥራ ላይ ሰሜናዊ ፈረንሳይ፣ እአአ ግንቦት 14/2024

ታጣቂዎች ዛሬ ማክሰኞ ኖርማንዲ ውስጥ በአንድ የእስረኞች ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት 2 የፈረንሳይ የማረሚያ ቤት ሰራተኞች ሲገደሉ ሌሎች 3 በጽኑ መቁሰላቸው ተዘግቧል። አንድ በጥብቅ የሚጠበቅ እስረኛ ማምለጡንም የማረሚያ ቤት ባለሥልጣናት ጨምረው አስታውቀዋል።

የእስረኞች ማመላለሻ ተሽከርካሪው ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ሞሃመድ አመራ የተባለውን እስረኛ ጉዳዩ ከተሰማበት የሩዋን ፍርድ ቤት ውሎ መልስ ወደ ኢቭሩ እስር ቤት በማጓጓዝ ላይ ነበር።

የፍትህ ሚኒስትሩ ኤሪክ ዱፖንድ-ሞሬቲ በአስቸኳይ ሁኔታው ለመርዳት የተፈጠረውን ቀውስ የሚከታተለውን ቡድን እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል።

"እነዚህን ወንጀለኞች አድነን ለመያዝ ሁሉም ዓይነት ዘዴዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው” ያሉት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጄራልድ ዳርማኒንም በኤክስ የማሕበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “በሰጠሁት መመሪያ መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖሊስ መኮንኖች እና ወታደራዊ ፖሊሶች ተንቀሳቅሰዋል" ብለዋል።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው "የእስር ቤት አስተዳደር ሰራተኞችን ህይወት የቀጠፈው የዛሬ ማለዳው ጥቃት ሁላችንንም አስደንግጦናል" ሲሉ ያደረባቸውን ስሜት ገልጠዋል።

ፈጽሟል በተባለው የስርቆት ወንጀል ሳቢያ በቅርቡ የተፈረደበት እና ጥብቅ ክትትል ይደረግበት የነበረው አምራ - የአቃቤ ሕግ ጠበቃው ሎወ ቢኪው እንዳስረዱት - ማርሴይ ውስጥ ፈጽሟቸዋል በተባሉ የአፈና እና የግድያ ወንጀሎች ጉዳይ ምርመራ ላይ ነበር።

አምራ - "ለሙሽ" .. በራሪው .. የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶት እንደነበር የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG