በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ ፖለቲካ ፓርቲዎች አሸናፊው ነጥሮ ባልወጣበት ምርጫ የበላይነት ለማግኘት የያዙትን ፉክክር አጧጡፈዋል


በፓሪስ ይርሚገኘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት፤ እአአ ነሃሴ 8/2024
በፓሪስ ይርሚገኘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት፤ እአአ ነሃሴ 8/2024

የትኛውም የፖለቲካ ኃይል ግልፅ አብላጫ ድምጽ ያላገኘበትን የትላንት በስቲያውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ፤ አገሪቱን የመምራት ሥልጣን ባለቤት ገና ባልለየበት፣ የፈረንሳይ ፓርቲዎች ዛሬ ማክሰኞ ጠንካራ ሆኖ ለመታየት እና አጋሮችን ለማሰብሰብ ጥረት ይዘዋል።

በምርጫው ያልተጠበቀ ውጤት ያስመዘገቡት ‘ኒው ፖፑላር ፍሮንት’ የተባለው የግራ ዘመም ጥምረት ተመራጭ የፓርላማ አባላት የሃገሪቱ ሸንጎ ከሚከፈትበት የፊታችን ሃምሌ 11 አስቀድሞ አዲሱን የሥራ ቦታቸውን እየጎበኙ ነው።

ይሁን እንጂ የአረንጓዴ፣ የሶሻሊስት፣ እና የኮሚኒስት እንዲሁም አክራሪው ግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት ‘ኤልኤፋፍአይ’ አባላት በበኩላቸው ማንን ጠቅላይ ሚንስትር ይሁን በሚለው እና ሰፊ ጥምረት መመስረት’ን በመሳሰሉ ሃሳቦች ዙሪያ አሁንም እየተከራከሩ ነው።

ግራ ዘመሙ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 577 መቀመጫዎች ካሉት ብሔራዊ ምክር ቤት በድምር 193 መቀመጫዎችን በመያዝ ከሁሉም ከፍ ያለ ድምፅ ቢያገኙም፤ መንግስት ለመሥረት የሚያስችላቸውን ባለ 289 አብላጫ መቀመጫ ግን ሳያገኙ ቀርተዋል።

ሆኖም የኤልኤፍአዩ’ መሪ ማቲልዴ ፓኖት እንዳስረዱት ግን የጥምረቱ አባላት እስከ ሳምንቱ መገባደጂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን የሚችለውን ሰው ለመሰየም ዕቅድ አላቸው።

በፈረንሣይ የፖለቲካ ሥርዓት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሾ’መው በፕሬዝዳንቱ ቢሆንም፤ የፓርላማውን የትምምን ድምፅ ማግኘት ስለሚሻ፤ ሶስት የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ተዋናይ በሆኑበት የፖለቲካ ምሕዳር ይህን መሰሉ ውጥን ቀላል ላይሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG