በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ መንግሥት በነዳጅ ጋዝ ላይ ሊያደርግ ያቀደውን የቀረጥ ጭማሬ ተወ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርዶ ፊሊፕ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርዶ ፊሊፕ

የፈረንሳይ መንግሥት በነዳጅ ጋዝ ላይ ሊያደርግ ያቀደውን የቀረጥ ጭማሬ ተወው ምክንያቱም፣ ዕቅዱን በመቃወም ፓሪስ ከተማ ውስጥ ለአያሌ ቀናት የዘለቀ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ነው፡፡

የፈረንሳይ መንግሥት በነዳጅ ጋዝ ላይ ሊያደርግ ያቀደውን የቀረጥ ጭማሬ ተወው ምክንያቱም፣ ዕቅዱን በመቃወም ፓሪስ ከተማ ውስጥ ለአያሌ ቀናት የዘለቀ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤድዋርዶ ፊሊፕ ዛሬ በብሔራዊው ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፣ አዲስ የታቀደው የቀረጥ ጭማሬ ለሚቀጥሉት ሥድስት ወራት እንዲዘገይ መደረጉን አስታውቀዋል።

ቀደም ሲል ግን እአአ በ2019 አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቀን ሥራ ላይ እንዲውል መታቀዱ ይታወቃል።

የሀገሪቱን ብሔራዊ አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል ቀረጥ አዋጭ ዕርምጃ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ይህንንም ተቃዋሚዎቹ ግልፅ አድርገውታል” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG