በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሣይና ጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሠላም ሂደቱን ለመደገፍ ኢትዮጵያ ይገኛሉ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይዋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎና እና ከጀርመኗ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክ ጋር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይዋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎና እና ከጀርመኗ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክ ጋር

የፈረንሣይና ጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። የጉብኝታቸው ዓላማም በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የተደረገውን ጦርነት ያስቆመውን የሠላም ስምምነት ለመደገፍ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይዋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎና እና ከጀርመኗ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክ ጋር በአንድ ላይ መገናኘታቸውን በማኅበራዊ ገጾቻቸው አጋርተዋል።

ጉብኝቱ የተደረገው የትግራይ አማጺያን በሠላም ሥምምነቱ መሠረት ከባድ መሣሪያዎቻቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት ባስረከቡ ማግስት መሆኑን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘገባ አውስቷል።

ሚኒስትሮቹ በሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአገሪቱ ባለሥልጣናት በተጨማሪ ከአፍሪካ ኅብረት መሪዎች እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት አራማጆች ጋር ይገናኛሉ። በተጨማሪም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ማከፋፈያ ማዕከልን ይመለከታሉ ተብሏል።

ካትሪን ኮሎና ከፈረንሳይ ከመነሳታቸው በፊት እንደተናገሩት የጉብኝታቸው ዓላማ “የሠላም ሂደቱን መደገፍ፣ ወንጀለኞች ተጠያቂ የመሆኑበትን እንዲሁም መልሶ-ግንባታን ለመደገፍ ነው” ብለዋል።

ኤኤፍፒ የዲፕሎማሲ ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው ሁለቱ ሚኒስትሮች ከአውሮፓ ኅብረት የተላከ መልከዕክት እንደያዙና፣ ይህም ኅብረቱ እንደገና ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን፣ ነገር ግን ተኩስ አቁሙ መከበር እንዳለበትና የሽግግር ፍትሕ መኖር እንዳለበት ኅብረቱ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG