በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ የጀርመን እና የጣሊያን መሪዎች በዩክሬን ጉብኝት ላይ ናቸው


ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ፣ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ በኪየቭ እአአ ሰኔ 16/2022
ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ፣ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ በኪየቭ እአአ ሰኔ 16/2022

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ እና የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የሩሲያን ወረራ በመመከት እየተዋጋች ላለችው ለዩክሬን ድጋፋቸውን ለመግለጽ ዛሬ ዋና ከተማዋ ኪየቭ ገብተዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ማክሮን "ከዩክሬን ህዝብ ጋር ያለንን አንድነት የሚገልጽ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ጉብኝት ነው” ብለዋል።

መሪዎቹ ወደኪየቭ የተጓዙት የአውሮፓ ኮምሽን በዩክሬን የአህጉራዊ ህብረት ዕጩነት ጉዳይ ላይ ስለሚሰጠው ምክረ ሃሳብ እየተነጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት ነው።

መሪዎቹ በኪየቭ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ጋር እንደሚገናኙ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ የምትልክ መሆኑን ትናንት ረቡዕ አስታውቃለች።

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ ስትሰጥ ይህ አስራ ሁለተኛው እና እስካሁን ከለገሰችው ሁሉ ግዙፉ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG