ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ከትላንት በስቲያ ከኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ ጉባኤ ለጋዜጠኛ ጥያቄ በሰጡት መልስ የዚያችን አገር መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንደተመረጠ አድርጎ መግለጻቸዉ ከብዙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ትችት አስከትሏል።
Freedom House የተባለዉ መሰረቱ እዚህ United States የሆነዉ ድርጅት ኢትዮጵያ ተገቢ ያልሆነ ሙገሳ ከUnited States ተትሮአታል ሲል መግለጫ አዉጥቷል።
ፕሬዚደንት ኦባማ ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ያሸነፈበትን ያለፈዉን ግንቦት የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስሊ መግለጻቸዉ መሰረታዊ ስህተት ነዉ ብለዋል Mark P Lagon የFreedom House ’ፕሬዚደንት። የኢትዮጽያን መንግስት በዴሞክራሲ የተመረጠ ብሎ መግለጽ የዴሞክራሲን ደረጃ ዝቅ ከማድረግም በተጨማሪ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የሚታገሉ የብዙ ኢትዮጽያዉያንን ጥረት እንደማኩሰስ ነዉ ብለዋል።
ፕሬዚደንት ኦባማ የኢትዮጽያን መንግስት በዴሞክራዊ የተመረጠ ብሎ መግለጻቸዉ እንዲሁ የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድርጅት የAmnesty Internationaln ና የHuman Rights Watch ንም ትኩረት ስቧል። ሁለቱም ድርጅቶች ፕሬዚደንቱ ተሳስተዋል በማለት መግለጫ አዉጥተዋል። በቅርቡ ከእስር ቤት የተፈታችዉ ጋዜጠኛ ርእዮት ዓለሙም፥ ለጋርዲያን ጋዜጣ በሰጠችዉ ቃለ ምልልስ ተገቢ ያልሆነ እዉቅና ለኢትዮጽያ መሪዎች በመስጠት ፕሬዚደንት ኦባማን ወቅሳለች።