ፈረንሣይ በሰሜን ሶሪያ ካምፖች የሚገኙ 35 ህጻናትና 16 እናቶቻቸውን ወደ ፈረንሳይ መመለሷን አስታወቀች፡፡
የፈረንሳይ የውጭ ጒዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ህጻናቱ ለማኅበራዊ ተንከባካቢ ድርጅቶች የተሰጡ ሲሆን የጤንነታቸው ሁኔታም ክትትል እንደሚደረግበት አስታውቋል፡፡
የእናቶቹ ጉዳይ ግን በፍርድ ቤት የሚይታይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
የሰአብዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች በዩናይትድ ስቴትስ እየተመሩ እስላማዊ መንግሥት ቡድኖችን የሚዋጉ አገሮች እስላማዊ መንግሥትን ወታደራዊ ቡድን ለመቀላቀል የሄዱትንም ሆነ በግጭቱ ወቅት እዚያ የተወለዱ ዜጎቻቸውን እንዲያስመልሱ አሳስበዋል፡፡