በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ መንግሥት የኮቪድ-19 ክትባት ያልወሰዱ የጤና ባለሞያዎች አገደ


ፎቶ ፋይል፦ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
ፎቶ ፋይል፦ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

የፈረንሳይ መንግሥት ከመስከረም 7/2014 ጀምሮ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባለማክበር የኮቪድ-19 ክትባትን ያልወሰዱ 3000 የሚደርሱ የጤና ዘርፍ ሰራተኞችን ማገዷን አስታወቀች፡፡

የፈረንሳይ ጤና ሚኒስትር ኦሊቭረ ቬራን ትናንት በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ 2.7 ሚሊዮን ከሚደርሱ የጤና ሠራተኞች ውስጥ በርከት ያሉ የጤና ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ክትባቱን ከመውሰድ ሥራ መልቀቁን የመረጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የመስከረም 7ቱን፣ የክትባት ግዴታ ቀነ ገደብ ባወጡትበት ወቅት፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የጤና ሠራተኞች ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እንኳ ያልወሰዱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

የጆን ሆፕኪንስ የኮሮናቫይረስ የምርምር ማዕክል ዛሬ ጧት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ፈረንሳይ ለኮቪድ-19 የተጋለጡ ከ7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሏት ሲሆን 116ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሞተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG