በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳዩ ወግ አጥባቂ መሪ አብላጫ ድምጽ ይፈልጋሉ


የፈረንሳይ ቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ መሪ ጆርዳን ባርዴላ
የፈረንሳይ ቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ መሪ ጆርዳን ባርዴላ

የፈረንሳይ ቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ መሪ ጆርዳን ባርዴላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ መያዝ የሚያስችላቸውን ቦታ ለማግኘት፣ ከተመደበለት ጊዜ ቀደም ብሎ እ.አ.አ በሰኔ 30 በሚካሄደው ምርጫ መራጮች አብላጫውን ድምፅ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

ከሕዝብ የተሰበሰቡ የቅድመ ምርጫ አስተያየቶች እንደሚያሳዩት ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከወግ አጥባቂዎቹ እና ከአዲሱ ግራ ዘመም ጥምረት ተከትለው በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር ምርጫ በፊት በቀራቸው ሁለት ሳምንት ልዩነቱን ለማጥበብ ከፍተኛ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

"ፍፁም የሆነ አብላጫ ድምፅ እፈልጋለሁ" ያሉት የ28 ዓመቱ የቀኝ አክራሪው ብሔራዊ ስብስብ ፓርቲ መሪ ባርዴላይ "የፕሬዚዳንቱ ረዳት መሆን አልፈልግም" ሲሉ የመገናኛ ብዙኅን ተናግረዋል።

በፓርላማ የነበራቸውን አብላጫ ድምጽ እ.አ.አ በ2022 ያጡት ማክሮን ሰኔ 30 የመጀመሪያው ዙር ድምፅ አሰጣጥ እንዲካሄድ የጠየቁ ሲሆን፣ ሁለተኛው ዙር እ.አ.አ በሐምሌ 7 ይካሄዳል።

በሰኔ 30 ለሚካሄደው ምርጫ ፓርቲያቸው እራሱን ከባህላዊው ቀኝ ዘመም ቡድን ጋር ያጣመረው ባርዴላ በቂ ድምፅ ማግኘት እና በፈንሳይ መንግሥት የመጀመሪያ ወጣቱ መሪ ለመሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "የታሪክን አካሄድ ለመለወጥ የሚያችል ታሪካዊ አጋጣሚ ነው" በማለትም ለመራጮች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG