በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሣይ እስረኛ ያስለቀቁ ታጣቂዎችን ፍለጋው ቀጥሏል


የእስር ቤቱ እይታ ከኮርባስ ማረሚያ ቤት ውጭ በተደረገው ተቃውሞ ተሰብሰበው፣ ሊዮ፣ ፈረንሳይ አአ ግንቦት 15/2024
የእስር ቤቱ እይታ ከኮርባስ ማረሚያ ቤት ውጭ በተደረገው ተቃውሞ ተሰብሰበው፣ ሊዮ፣ ፈረንሳይ አአ ግንቦት 15/2024

በፈረንሣይ ትላንት አንድ እስረኛን አጅበው በሚሄዱ ሄዱ ጠተባቂዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ሁለቱን ገድለው ሦስቱን በማቁሰል እስረኛውን ያስመለጡት ታጣቂዎችን ፍለጋ መቀጠሉ ታውቋል።

ከአደንዛዥ እፅ ጋራ በተያያዘ ግድያ ተይዞ የነበረውንና ሞሃመድ አምራ የተባለውን ግለሰብንም ሆነ አስመላጮቹን ለመፈለግ ብዛት ያለው ኃይል መመደቡን የፈረንሣይ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል። ድርጊቱ ፈረንሣይን እጅግ እንዳስደነገጠ በመነገር ላይ ነው።

ጥቃት የፈፀመው ታጣቂ ቡድን እንደሚያዝና ዋጋ እንደሚከፍልበትም የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዝተዋል።

ከእስር ያመለጠው የ30 ዓመቱ ሞሃመድ አምራ፣ ዘረፋን ጨምሮ በ13 ወንጀሎች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ወንጀል የፈፀመው የ15 ዓመት ልጅ ሳለ እንደነበር አቃቢያነ ሕግ አስታውቀዋል።

ጥቃት አድራሾቹ የእስረኞች ማመላለሻ ተሽከርካሪው ሲወጣ ጠብቀው ከያዙት መኪና ጋራ በማጋጨትና ቀጥሎም ተኩስ በመክፈት እስረኛው እንዲያመልጥ አድርገዋል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG