በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ አምባሳደሯንና ጦሯን ከኒዤር እንደምታስወጣ አስታወቀች


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን

ፈረንሳይ፣ በኒዤር የሚገኙ አምባሳደሯን በሰዓታት በሚቆጠር ጊዜ ውስጥ እንደምታስወጣና በቀጣይ ወራትም፣ በአገሪቱ ያሰፈረችው ጦሯን እንደምታስወጣ፣ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን፣ ትላንት እሑድ አስታውቀዋል።

ውሳኔውን በመልካም እንደተቀበሉት የጠቀሱት የኒዤር ወታደራዊ መሪዎች፣ “ሉዓላዊነትን ለማስከበር አንድ ርምጃ ወደፊት ለመሔድ የሚያስችል ነው፤” ሲሉ ገልጸውታል።

“ከኒዤር ጋራ ያለው ወታደራዊ ትብብር አብቅቷል፤”

“ከኒዤር ጋራ ያለው ወታደራዊ ትብብር አብቅቷል፤” ያሉት ማክሮን፣ ወታደሮቻቸውን የማስወጣት ሥራው፣ እስከያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።

አፍቃሬ ፈረንሳይ እንደኾኑ የሚነገርላቸው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙም፣ ከሁለት ወራት በፊት፣ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወግደዋል።

ትላንት እሑድ፣ የኒዤር ወታደራዊ መሪዎች፣ የፈረንሳይ አውሮፕላኖች በሀገሪቱ የአየር ክልል እንዳይበሩ አግደዋል።

ፈረንሳይ 1ሺሕ500 የሚደርስ ጦሯን በኒዤር ያሰፈረችው፣ “በሳህል የሚንቀሳቀሱ ጂሃዲስቶችን ለመዋጋት” በሚል ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG