በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይና የአሜሪካ ድርጅቶች ለደን ጥበቃ 100 ሚሊዮን ዩሮ መደቡ


የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ በጋቦን
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ በጋቦን

ፈረንሳይና ሁለት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሞቃታማው የዓለም ክፍል የሚገኘውን የተፈጥሮ ደን ለመጠበቅ እንዲውል በድምሩ 100 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚለግሱ አፍሪካን በመጎብኘት ላይ ያሉት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታውቀዋል።

የተፈጥሮ ሃብት የኢኮኖሚያቸው ዋናውን ክፍል እንዲይዝ እንደሚሹ ማክሮን በጋቦን በደን ጉዳይ ላይ ሲመክር በነበረ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተናግረዋል።

በሞቃታማው የዓለም ክፍል የሚገኘውን ደን ለእርሻ እና ለግንባታ መመንጠር አስጊ ሁኔታ መፍጠሩንና ይህም ለአየር ንብረት መለወጥና በውስጡ ለሚኖሩ እጽዋትና እንሣሳት ሕይወት አደገኛ ሁኔታ መፈጠር ምክንያት ሆኗል ሲል ኤኤፍፒ በሪፖርቱ ጠቁምሟል።

“ደናቸውን ለመጠበቅ ለሚሹ አገራት 100 ሚሊዮን ዩሮ መድበናል” ብለዋል ማክሮን በጉባኤው ላይ ሲናገሩ።

ፈረንሳይ ግማሹን ገንዘብ ስትሸፍን፣ ‘ኮንሰርቬሽን ኢንተርናሽናል” ከተሰኘ ትርፋማ ካልሆነ አሜሪካዊ ድርጅትና “ዎልማርት” ከትሰኘው ትልቁ የአሜሪካ የሸቀጥ መደብር ቀሪውን ግማሽ ይሸፍናሉ ብለዋል ማክሮን።

XS
SM
MD
LG