በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስደተኞችን ከጎዳና ወደመጠለያ ማስገባት ተጀመረ


ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ
ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ

በመቶዎች የተቆጠሩ የፈረንሣይ ፖሊሶች ዋና ከተማ ፓሪስ ሰሜን ምሥራቅ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ የሆነ የፍልሰተኞች ካምፕ ዛሬ ማፈራረስ ጀምረዋል።

የፈረንሣይ መንግሥት ስደተኞችን ከጎዳናዎች አንስቶ ወደመጠለያዎች ለማስገባት እየተንቀሳቀሰ ነው።

የረድዔት ድርጅቶች እንደሚናገሩት በስታሊንግራድ እና ዦሬ በሚባሉት የከተማ ባቡር ጣቢያዎች መካከል ባለው መሿለኪያ ጠርዝ ጠርዙን ይዞ ባለው ካምፕ ወደሶስት ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች ተጠልለው ቆይተዋል።

ዛሬ ብዛት ያላቸው ፍልሰተኞች ዕቃቸውን ሸክፈው በትክክል ወደሚመዘገቡበት ማዕከል የሚወስዱዋቸውን አውቶብሶች ሲጠብቁ ታይተዋል።

የፈረንሣይ የኢሚግሬሽን መ/ቤት ኃላፊ ዲዲየር ሌስሺ በመመዝገቢያው ጣቢያ አስተርጓሚዎችን ይዘን ፍልሰተኞቹን እንጠብቃለን ብለዋል።

ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ
ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ

“መጀመሪያ ወደማዕከሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ተቀብለናቸው፤ ከዚያም ጥገኝነት ለመጠየቅ እንዴት ማመልከቻ እንደሚሞሉ እናስረዳቸዋለን” ብለዋል።

በየድንኳኑ አለዚያም ከቤት ውጭ ፍራሽ ላይ የተኙትን ስደተኞች ዛሬ ፖሊሶች በሌሊት ሄደው ሲቀሰቅሱዋቸው

“በዚህ ውድቅት የት ልንሄድ ነው” ብለው ተደናግጠዋል።

ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ
ስደተኞች በፈረንሣይ ስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ

በዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ከተካሄዱት ግዙፍ የስደተኛ መጠለያ ማስገባት ኦፐሬሽኖች ትልቁ መሆኑን የባለስልጣናት ገልፀዋል።

የስታሊንግራድ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ስደተኞችን አንስተዋቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ መጪዎች ሰፍረው ቆይተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ስደተኞች ከጎዳና ወደመጠለያ ማስገባት ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00

XS
SM
MD
LG