በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ ፕሬዛዳንት ኢራቅ ገብተዋል


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በሞሱል ኢራቅ
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በሞሱል ኢራቅ

የፈረንሳይ ፕሬዛዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ለጉብኝት ኢራቅ ገብተዋል፡፡

ሰሜን ኢራቅ በምትገኘውና ከአይሲስ ጋር በተደረገው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባት ሞስል ከተማ የገቡት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት አገራቸው ከኢራቅና ከክልሉ የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሽብርተኝነትን በጋራ እንደሚፋለሙ ተናግረዋል፡፡

የኢራቅ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው ሞስል ጉብኝት ያደረጉት ማርኮን እኤአ በ2014 በአይሲስ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበትን የካቶሊክ ቤተከርስቲያን ጎብኝተዋል ሲል አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG