በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመርያው ክፍል የአውሮፓ ህብረት ግብረ-ሀይል ሳህል ገባ


ግብረ ሃይሉን የመመስረት እቅድ የወጣው ከሁለት አመትት በፊት ሲሆን በቀጠናው አለም አቀፍ ወረርሽኝ፣ የፖለቲካ ትርምስና መነሳሳት እየተስፋፋ ባለበት ሁኔታ መድረሱ ተገልጿል።

የመጀምርያው የታኩባ ክፍል አካል በመሆን የገቡት 100 የኢስቶንያና የፈረንሳይ ወታደሮች ናቸው። በመጪው ጥቅምት ወር ደግሞ 60 የቼክ ወታደሮች ይገባሉ ተብሏል።

ከጥቂት ወራት በሁዋላም 150 የስዊድን ወታደሮች እንደሚቀላቀሉ ታውቋል። ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮችም ወታደሮች እንደሚልኩ ተገልጿል። አላማው ማሊና ኒጀር በቀጠናው ያሉትን የእስላማዊ አመጽ ቡድኖችን እንዲታገሉ ለመርዳት መሆኑ ታውቋል።

እስካሁን ባለው ጊዜ በዋናነት በቀጠናው ወታደሮች ስትልክ የቆየችው ፈረንሳይ ናት። 5,100 የሚሆኑ የፈረንሳይ ወታደሮች ለሰባተኛ አመት ሳሕል እንደሰፈሩ ተንታኞች ገልጸዋል።

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG