በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይና እንግሊዝ የክትባት ስርጭታቸውን ጨመሩ


በኮሮናቫይረስ ልውጥ ዝርያዎች የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ፈረንሳይና እንግሊዝ የክትባት ስርጭታቸውን መጨመራቸውን አስታውቀዋል።

ፈረንሳይ ሁሉም አዋቂዎች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ አድርጋለች። ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ በቫይረሱ ተይዘው ያገገሙት ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እርሳቸው እና ባለቤታቸው ብሪጂት ክትባቱን ሰኞ ለት ከወሰዱ በኋላ በትዊተር የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት

"ልክ እንደ እኔና እንደ ብሪጂት፣ ወይም ልክ እንደ ሌሎች 25 ሚሊዮን ፈንሳውያን እንዳደረጉት እንከተብ። እራሳችንና የምንወዳቸውን ሰዎች ከበሽታው እንጠብቅ።" ብለዋል።

እሰከ ሰኞ ባለው ጊዜ ድረስ በፈረንሳይ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5.7 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 109 ሺህ 690 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ የኮሮና ቫይረስ መረጃ ማዕከል ያሳያል።

በተመሳሳይ እንግሊዝም የለንደኑን ትዊክንሃም የራግቢ መጫወቻ ሜዳ ለክትባት ዘመቻ ክፍት ማድረጓን የጤና ሀላፊዎች አስታውቀዋል። ክትባቱን ለመውሰድ ምንም ቀጠሮ አያስፈልግም። በህንድ በተገኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ዝርያ ምክንያት እየጨመረ የሄደውን በቫይረሱ የሚያሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለችው እንግሊዝ እስካሁን 4.5 ሚሊዮን የኮቪድ ተያዦች እንዳሏትና 128 ሺህ 44 ሰዎች ለህልፈት እንደተዳረጉ አረጋግጣለች።

ጀርመንም ከመጪው ሰኔ 7 ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች በሙሉ መሰጠት እንደሚጀምር አስታውቃለች። በጀርመን በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን የደርሰ ሲሆን 88 ሺህ 469 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

XS
SM
MD
LG