በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሣይ በኒጀር የሚገኘው ኤምባሲዋን ዘጋች


የኒጀር ብሄራዊ ፖሊሶች ኒጀር የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ እያለፉ
የኒጀር ብሄራዊ ፖሊሶች ኒጀር የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ እያለፉ

ፈረንሣይ ሌላ ተጨማሪ ማብራሪያ እስኪሰጥ ድረስ በኒጀር የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘግታለች ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል።

ውሳኔው የተሰጠው የፓሪስ ቁልፍ አጋር በሆነችው ኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የመጨረሻዎቹ የፈረንሣይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ከወጡ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡

“በኒጀር የሚገኘው የፈረንሣይ ኤምባሲ ተከታዩን እስኪያስታውቅ ድረስ ተዘግቷል” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ቢገልጽም፣ ልዑኩ ከፓሪስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ግን እንደሚቀጥል ገልጿል።

መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ ወዲህ ላለፉት አምስት ወራት "ኤምባሲያችን ከባድ መሰናክሎች አጋጥመውታል ይህም ተልዕኮውን ለመፈፀም የማይቻል ያደርገዋል" ሲል በተልዕኮው ዙሪያ የገጠሙትን ችግሮች አመልክቷል፡፡

በአዲሶቹ ወታደራዊ መሪዎች የተባረሩትን የፈረንሣይ አምባሳደርን ጨምሮ፣ አብዛኞቹ የኤምባሲው ሠራተኞች ከተወሰነ ጊዜ በፊት ለቀው መውጣታቸው በኤኤፍፒ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

ወታደራዊው መንግሥት እኤአ ሀምሌ 26 የተመረጡትን የሀገሪቱ መሪ መሀመድ ባዙምን ከስልጣን ያስወገደ ሲሆን፣ ከፈረንሳይ ጋር የነበረውን የመከላከያ ስምምነቶችን ሰርዟል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባዙም በኒያሚ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን ባለፈው ጥቅምት እንደተናገሩት ዋሽንግተን ወደ 1,000 የሚጠጉ ወታደሮችዋን በኒጀር እንደምታቆያቸው ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግን የኒጀር ኃይሎችን እያሰለጠነች ወይም እየረዳች አይደለም ሲሉ ባለሥልጣኑ አክለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG