በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪዋ ማሪን ለ ፔን እአአ ሚያዝያ 24 ቀን የመጨረሻ ዙር ፉክክራቸውን ያካሂዳሉ።
ትናንት በመጀመሪያው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ዘጠና ከመቶው ድምጽ ተቆጥሮ ማክሮን ሃያ ሰባት ከመቶ ለ ፔን ሃያ አራት ከመቶ አግኝተዋል። ማክሮን የነበራቸው ደልደል ያለ የመራጭ ድጋፍ ምርጫው እየተቃረበ ሲሄድ እየተነነ መሄዱ ተስተውሏል። ለ ፔን የኑሮ ውድነት ጉዳዮችን በማንሳት የምረጡኝ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ በመጨረሻ ደቂቃ የመራጭ ድጋፍ እንደጨመረላቸው ተዘግቧል። ጸረ ኢሚግሬሽን አቀንቃኝነታቸውን የአውሮፓ ህብረት ነቃፊነታቸውን ለዘብ ሊያደርጉም ሞክረዋል።
ፕሬዚዳንት ማክሮን በተለይም ከዩክሬኑ ጦርነት በተያያዘ ስራ እንደበዛባቸው በመግለፅ ምረጡኝ ዘመቻ ውስጥ የገቡት ዘግይተው ነው።