የአዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ "ተራማጅ ሪፐብሊክ" ትናንት በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ የመጀመሪያ ዙር በከፍተኛ ድምፅ አሸንፏል።
መሃልተኛው የፈረንሣይ "ተራማጅ ሪፓብሊክ" (ሬፕዩብሊክ ኧን ማርሽ) ፓርቲ በሌሎች ሁለት ዋና ዋና ፓርቲዎች ላይ ባገኘው ያልተጠበቀ ድል የፕሬዚደንት ማክሮን ፓርቲ አጀንዳዎቹን በምክር ቤቱ ውስጥ በቀላሉ እንዲያሳልፍ ዕድል ከፍተውለታል።
አጠቃላዩ የድምፅ ሰጭ ቁጥር መቀነስ ሕዝቡ በፖለቲከኞች ላይ ያለው አመኔታም መቀነሱን እንደሚጠቁም ተነግሯል።
ለትናንቱ ምርጫ የወጣው የድምፅ ሰጭ ቁጥር ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ48 ከመቶ ያነሰ ነበር።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ