በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ በአፍሪካና አውሮፓ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየታገለች ነው


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

ፈረንሳይ በአፍሪካና በአውሮፓ አገሮች ውስጥ የሚኖራትን ተጽዕኖ ለማሳደግ የምታደርገው ጥረት የድብልቅ ስሜት መፍጠሩ ተነገረ፡፡

የአፍሪካና የፈረንሳይን ግንኙነት ወደነበረት ለመመለስ ለሚያደርጉት ጥረት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚህ ዓመት በአራት የማዕከላዊ አፍሪካ አገሮች ያደረጉት ጉብኝት የተለያየ ስሜት መፍጠሩ ተነግሯል፡፡

በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው አውሮፓ የሚኖራት ተጽእኖ የዩክሬኑን ጦርነትና ከባህር ማዶ እያደገ በመጣው የሩሲያ ተጽዕኖ ሳቢያ እጅግ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አስቸጋሪ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ማክሮን ባላፈው መጋቢት ወር ወስጥ በማዕከላዊ አፍሪካ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋቦን እና አንጎላን ቢጎበኙ ሁሉም እንደተፈለገው በቀላሉ የተጠናቀቀላቸው አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

ማክሮን የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ባልነበረችው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያደረጉት ጉብኝት ተቃውሞ የገጠመው መሆኑም ተነግሯል፡፡

ማክሮን ባለፈው የካቲት አፍሪካን አስመልክቶ ያወጡት ፖሊሲ በአህጉሪቱ ያሰማሩትን የጦር ኃይል በመቀነስ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ ግንኙነትን መፍጠር የሚል ነበር፡፡

ማክሮን አውሮፓ ራሱን የቻለ የመከላከያ ኃይል ይኑራት በሚል ያራመዱት ሃሳብም ብዙም ያልተሳካላቸው መሆኑን ተችዎች ይናገራሉ፡፡

አውሮፓ ውስጥ በዩክሬኑ ጦርነት የተነሳ የኃይል ሚዛኑ ከታወቁት ምዕራባውያኑ የፈረንሳይና ጀርመን ውጭ፣ በሩሲያ ላይ ጠንካራ አመለካከት ወዳላቸው እንደ ፖላንድ የመሳሰሉ የምሥራቅ አውሮፓ አግሮች እያዘነበለ መሆኑንም ተንታኞች አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG