በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍልስጤም የእስራኤልና እስላማዊ ጅሃድ ተኩስ አቁም ንግግር


እስራኤል ባለፈው ሳምንት በጋዛ ከተማ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የፈራረሱ ህንፃዎች እአአ ኦገስት 8/2022
እስራኤል ባለፈው ሳምንት በጋዛ ከተማ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የፈራረሱ ህንፃዎች እአአ ኦገስት 8/2022

ፍልስጤም ውስጥ በእስራኤልና በእስላማዊ ጅሃድ ታጣቂዎች መካከል ብዙም “ጠንካራ አለመሆኑ” የተነገረለት የተኩስ አቁም ሥምምነት መካሄዱ ተነገረ፡፡

በግብጽ አደራዳሪነት ዛሬ ማለዳ መቀጠሉ የተነገረው ድርድር ተስፋ ማሳደሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በአገሬው አቆጣጠር እሁድ ከሰዓት በኋላ 5፡30 ላይ የተጀመረው ድርድር ሁለቱም ወገኖች ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን ስማቸውን እንዳይገለጽ የፈለጉ የግብጽ የደህንነት ባለሥልጣን ለአሶሼይትድ ፕሬስ መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡

የተኩስ አቁም ንግግሩ በትንሹ 15 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 44 ፍልስጤማውያን የሞቱበትን ያሁኑን ከባድ ግጭት ሊያቆመው እንደሚችል ተስፋ ማሳደሩም ተመልክቷል፡፡

የአሁኑ ግጭት ባላፈው ዓመት 11 ቀን ከፈጀውና የፍልስጤምን የባህር ዳርቻ ግዛት ካወደመው አስከፊው ጦርነት ወዲህ የተካሄደ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ግጭቱ የተቀሰቀሰው እስራኤል አንድ የጅሃድ ባለሥልጣንን በቁጥጥር ስር በማዋሏና የ17 ዓመት ፍልስጤማዊ በመገደሉ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በተያያዘ ዜና የቻይና፣ ፈረንሳይ፣ አይርላንድ፣ ኖርዌና፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛው ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዝግ ስብሰባ እንዲደረግ መጠየቃቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG