በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት የተመድ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ማሊ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የተመድ ትናንት በሰጠው መግለጫ፣ ሁለት የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ማዕከላዊ ማሊ ውስጥ መኪናቸው በተጠመደ ፈንጂ ላይ ሲጓዝ ሕይወታቸው ማለፉን አስታወቀ።

የተመድ ትናንት በሰጠው መግለጫ፣ ሁለት የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ማዕከላዊ ማሊ ውስጥ መኪናቸው በተጠመደ ፈንጂ ላይ ሲጓዝ ሕይወታቸው ማለፉን አስታወቀ።

ወታደሮቹ አደጋው የደረሰባቸው በቅኝት ላይ እንዳሉ ሲሆን፤ በዚሁ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሌሎች አራት የሰላም አስከባሪዎች ላይም የመቁሰል አደጋ መድረሱን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል።

የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፌነኢ ዱጃሪክ ስለሁኔታው በተናገሩት ቃል፣ የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ ልዩ ተወካይ ማሃማት ሳልህ አናዲፍ ጥቃቱን አውግዘው፣ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦችም የማፅናኛ ቃልና፣ ፈጣን ለሆነ ፈውስም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ብለዋል።

እአአ ከ2013 ዓ.ም ወዲህ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር የተመድ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት፣ አክራሪ እስልምናን እና በአጠቃላይ ህገወጥ ድርጊቶችን ለመቋቋም ማሊ ውስጥ መስፈሩ ይታወቃል።

ባለፈው ማክሰኞም ሥድስት የማሊ ወታደሮች መኪናቸው ማሊ ውስጥ በሚገኝ ተመሳሳይ ክልል ፈንጂ ላይ ሲጓዝ መሞታቸው ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG