ዋሺንግተን ዲሲ —
እስራኤል እና ጋዛ ድንበር አጥር አቅርቢያ ትናንትና ቅዳሜ ቦምብ ፈንድቶ አራት የእስራኤል ወታደሮች ቆሰሉ።
ሁለቱ በጽኑ መቁሰላቸው ተነገረ።
ፍንዳታውን ተከትሎ እስራኤል በስድስት የፍልስጥኤም ታጣቂ ዒላማዎች ላይ ትናንቱኑ የአየር ድብደባ አድርሳለች። ከተደበደቡት ዒላማዎች መካከል የጦር መሳሪያ ማምረቻ እየተገነባ ያለ ወደእስራኤል የሚወስድ የምድር ውስጥ መሿለኪያ እንደሚገኙበት የእስራኤል የጦር ሰራዊት ገልጿል።
በአየር ጥቃቱ ሁለት ፍልስጥኤማውያን መቁሰላቸውን የፍልስጥኤማዋያን የህክምና ምንጮች ገልጸዋል።
እስራኤልን በሃማስ ቁጥጥር ሥር ካለው የጋዛ አካባቢ በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ ለደረሰው ፍንዳታ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ የለም፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ