በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የትዊተር መልእክት

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ቅዳሜ በቨርጂንያ ክፍለ ግዛት በምትገኘው ሻርለትስቪል ከተማ ላይ ግጭት ከተከሰተ በኋላ አንድ ምስል ትዊተር ላይ አውጥተዋል። በማኅበራዊ ሚድያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተወዳጅነት አትርፏል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ቅዳሜ በቨርጂንያ ክፍለ ግዛት በምትገኘው ሻርለትስቪል ከተማ ላይ ግጭት ከተከሰተ በኋላ አንድ ምስል ትዊተር ላይ አውጥተዋል። በማኅበራዊ ሚድያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተወዳጅነት አትርፏል።

ባራክ ኦባማ በትዊተር ያወጡት ምስል ኮታቸው አንደኛው ትከሻቸው ላይ ጣል ብሎ እጃቸው ደግሞ መስኮት ላይ ተደግፎ በተከፈተው መስኮት በኩል አንቃራው የሚያይዋቸውን የተለያየ ዘር ያላቸው ሕፃናት ልጆችን ይመለከታሉ።

በምስሉ ሥር

“ሰዎችን በቆዳ ቀለማቸው፣ በማንነታቸው ወይም በሀይማኖታቸው ምክንያት የሚጠላ ሆኖ የሚወለድ ማንም ሰው የለም” የሚለውን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ጥቅስን አስፍረዋል።

ከዛሬ ንጋት አንስቶ የኦባማ የትዊተር መልእክት 2.8 ሚልዮን ጊዜ ተመልካችና አንባቢ አግኝቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG