በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክል ፍሊን ከሩስያ ጋር በመተባበር የሚደረግ የአሜሪካ ዕቅድ

ማይክል ፍሊን
ማይክል ፍሊን

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ጥር ወር የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለመሆን አሥራ አንድ ደቂቃ ሲቀራቸው ማይክል ፍሊን በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ማለት የምክር ቤት ህንፃ ደረጃ ላይ ሆነው ከሩስያ ጋር በመተባበር የሚደረግ የአሜሪካ ዕቅድ እንዲጀመር ለአንድ የቀድሞ የንግድ ተባባሪያቸው /ቴክስት/ ማድረጋቸውን አንድ ስው ማጋለጡ ታውቋል።

አሜሪካ ከሩስያ ጋር በመተባበር በመካከለኛው ምሥራቅ የኑክሌር ኃይል ስለመገንባት ዕቅድዋ ነበር ፍሊን “ሊጀመር ይችላል” የሚል /ቴክስት/ የላኩት።

ሚስጢሩን ያወጣው ሰው እንደሚለው ሩስያ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ውስጥ እጅዋን በመዶልዋ ምክንያት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጣሉባት የማዕቀብ ሕግ ይቀደዳል ሲሉ ማይክል ፍሊን ለቀድሞው የንግድ ተባባርያቸው አረጋግጠዋል።

ይህን ጉዳይ ትላንት ይፋ ያደረጉት በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምርያ ምክር ቤት የቁጥጥር ኮሚቴ አንጋፋ ዲሞክራት የሆኑት ኤልጃህ ከሚንግስ ናቸው።

ትራምፕ ሥልጣን ከማያዛቸው በፊት ዋሽንግተን ከነበሩት የሩስያ አምባሳደር ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ፍሊን በፌደራል መርማሪዎች በተጠየቁብት ወቅት፣ ዋሽተው እንደነበር አምነው ከተቀበሉ አንድ ሣምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው ይህ ምስጢር የወጣው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG