በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-በሽር ፍ/ቤት ቀረቡ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦመር አል-በሽር
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦመር አል-በሽር

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦመር አል-በሽር ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ለስልጣን ካበቃቸው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተመሰረተባቸው ክስ ዛሬ ካርቱም ላይ ያስቻለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ባለፈው ዓመት በሃገርቀፍ ተቃውሞ ተወጥረው ከሥልጣን የተወገዱት በሽር በሙስና ወንጀል በተፍረደባቸው የ2ዓመት እስራት ቅጣት እስር ላይ ናቸው።

ከወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥቱ በተያያዘ ሌሎች አስራ ስድስት ሰዎችም ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የሰባ ስድስት ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሃገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የሽግግር መንግሥት በዓለምቀፍ ማኅበረሰብ ተቀባይነት ለማግኘት የለውጥ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ነው።

ሱዳን አልበሽርን በዳርፉር ግጭት በተፈጸሙ የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀል ክሶች ለሚፈልጋቸው ለዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት አሳልፋ ልትሰጣቸው ቃል ገብታለች።

XS
SM
MD
LG